ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጉርድ ሾላ ያለውን ሕንጻና እንዲሁም ብሔራዊ ሆቴል ሕንጻን ውስጡን ቻክ አድርጎ ቀለም ለማስቀባት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጉርድ ሾላ በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ቢሮ እና እስጢፋኖስ ፊት ለፊት በሚገኘው የቀድ

ሞው ብሔራዊ ሆቴል ሕንጻ በአካል በመገኘትና በማየት፡-

  • በውሃ የሚበጠበጥ ቀለም በካሬ ­­­­_______________፤
  • ሴንቴቲክ (የፕላስቲክ ቀለም) በካሬ ሜት­­­­ር ____________ ዋጋ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡

ስለዚህ በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ ፤የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ የጨረታውን ሰነድ በኤንቨሎፕ ፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይችላሉ፤
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን ዋናና ቅጅውን በኤንቨሎፕ ፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሰባት (7) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 0116-47-97-94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፡፡

Download the pdf