የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት

ፕሬዝዳንት፡  ኢ/ር ዮናስ አያሌው
ተ/ም/ፕሬዝዳንት፡  አቶ ብርሀኑ መኮንን
ም/ፕሬዝዳንት፡  አቶ ብርሀኑ መኮንን
አቃቢ ንዋይ፡ ወ/ሮ ሰላማዊት ወንድማገኘሁ
አባል፡ ኮ/ር አበበ መኮንን
አባል፡ ሻ/ል ቶሎሳ ቆቱ
አባል፡ አቶ ወንዳለ ስጦቴ
አባል፡ አቶ ስምረቱ አለማየሁ
የፌ/ጽ/ቤት ኃላፊ፡ አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ እንቅስቃሴ መነሻ

የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ስፖርት እንቅስቃሴና ውድድር ታሪክ የሚጀምረው ከት/ቤቶች መቋቋም መስፋፋት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡
ከ1917 – 1928 በርካታ ትም/ቤቶች መከፈትና በነዚህም ት/ቤቶች መካከል የእርስ በርስ ውድድር በጊዜው በነበሩ ትም/ቤቶች ማለት ዳ/ምኒሊክ ፣ በተፈሪ መኮንን ፣ በእቴጌ መነንና በኮከበ ጽብሐ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መደረጉ የአትሌቲክስ ስፖርት እንዲስፋፋ በር ከፍቷል፡፡ ከዚያም በሸዋ ክ/ሀገርና በአ/አበባ ከተማ ያሉ ተቋማት የአትሌቲክስ ውድድር ይመራ የነበረው በክ/ሀገሩ ስፖርት መምሪያ ሥር ነበር፡፡
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የመጀመሪያው የጠቅላይ ግዛቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተዘጋጀው በ1971 ዓ.ም በ14ቱ ጠቅላይ ግዛቶች መካከል ሲሆን አ/አበባ በሸዋ ጠ/ግዛት ሥር ስለነበር በውድድሩ ተሳታፊ ሆኗል፡፡
በ1974 ዓ.ም በተደረገው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድር በአዲስ አበባ የሚገኙ 7 ቡድኖች (ክለቦች) ተሳታፊ ሆነው የማዕከላዊ እዝ፣ ምድር ጦርና አየር ኃይል ክለቦች ከ1ኛ – 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውጤት አስመዝግቦአል፡፡ በዚህ ውድድር በክፍለ ሀገር ደረጃ 10 ክፍለ ሀገሮች ሲሳተፉ አ/አበባ ምርጥ ቡድን አላሳተፈም፡፡
የአ/አበባ አትሌቲክስ ምርጥ ቡድን በኢትዮጵያ ሻምፒዮና መሳተፍ የጀመረው በከተማው ስፖርቱን የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ተጠሪ ጽ/ቤት እንደተቋቋመ ሲሆን በ1975 ዓ.ም እንደተቋቋመ የአትሌቲክስ ኮሚቴ በሥሩ 50 ክለቦች በማቋቋም ውድድሮችንና የከተማውን ምርጥ ቡድን በማዘጋጀት ከክ/ሀገር ምርጥ ቡድኖች ጋር ከ1975 እስከ 1989 በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፎ በሴትም በወንድም በተከታታይ በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ ሆኗል፡፡ በወቅቱም የከተማውን ምርጥ ቡድን ይወክሉ የነበሩት ክለቦች መቻል ፣ ባንኮች፣ ኦሜድላ፣ መብራት ኃይል ፣ ማረሚያ ቤቶች ፣ ንብና ኢትኮባ ከመሳሰሉት ክለቦች ምርጥ ቡድኑን በማዘጋጀት ነበር፡፡

የአ/አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አደረጃጀትና

እንቅስቃሴዎቹ

የአ/አበባ  አትሌቲክስ  ፌዴሬሽን በ1974 ዓ.ም  ከተቋቋመበት ጊዜ

ጀምሮ  የተለያዩ  የውድድር መርሀ   ግብሮች በመዘርጋት በርካታ

ክለቦችና ክፍለ ከተሞች ት/ቤቶችና የግል ተወዳዳሪዎችን በማሳተፍ የአትሌቲክስ  ስፖርት አሁን  ያለበት  ደረጃ  እንዲደርስ የበኩሉን

አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ፌዴሬሽኑ  ቀደም  ሲል 7 አባላት ባሉት  የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

ስራውን  ሲመራ  የቆዬ ሲሆን  በወቅቱ  የነበረውን  የአትሌቲክስ

አሰልጣኞና   ዳኞችን  እጥረት   ለማቃለል  በሙያው  ኮርሶችን

/ ስልጠናዎችን /   በመስጠት  የነበረበትን  የባለሙያዎች እጥረት

ለማቃለል ችሏል፡፡

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የራሱ የሆነ ጽ/ቤትና የመሰብሰቢያ

አዳራሽ ያልነበረው በመሆኑ  ይህንኑ ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ

ለመቅረፍ  ከሞሐ የለስላሳ መጠጦች  ኢንዱስትሪ  አክሲዬን ማህበር

በተደረገለት የገንዘብ ድጋፍ በ1991 ዓ.ም አሰርቶ በስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

ፌዴሬሽኑ በተለይም  ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ የስራ  አስፈፃሚና የቴክኒክ ኮሚቴውን  በማጠናከር  በወቅቱ   እንዲደራጁ  በተደረጉት  5  የ1ኛ

ዲቪዚዬንና  7  የ 2ኛ  ዲቪዚዬን  ክለቦች   መካከል   የአትሌቲክስ

ውድድሩን ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ከ 1994 – 1996 ዓ.ም  መጨረሻ   ድረስ   ፌዴሬሽኑ   የፋይናንስ

አቅሙን ለማጐልበት ከብሄራዊ  የኤች  አይ  ቪ  ኤድስ  መከላከያና

መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት  ጋር  በተደረገው  ስምምነት  መሰረት  የግንዛቤ

ማዳበሪያ ውድድሮች በአ/አበባና በክልል ከተሞች በማካሄድ ተገቢው የቅስቀሳ ስራ ተካሂዷል፡፡

የፌዴሬሽኑ የተሳትፎ እንቅስቃሴ  እየጐለበት በመሄዱ በ1996  ዓ.ም

መጨረሻ ላይ የክለቦች ብዛት ወደ 31 ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡ ይህም

በየክለቡ ተመዝግበው ለመሳተፍ ጥረት የሚያደርጉትን አትሌቶች ብዛት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር አድርጐታል፡፡

የአ/አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከጊዜ ወደ ጊዜ አቅሙን በማሳደግና ውድድሮችን በማስፋት በአለፍት ዓመታት የሀገራችንን ስም በዓለም ያስጠሩና የሀገራችን ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረጉ ታዊቂ አትሌቶች እንደነ መሰረት ደፋር፣ ሚሊዬን ወልዴ እና ሌሎችንም ታዳጊና ተተኪ አትሌቶችን በማፍራት ሀላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ፌዴሬሽኑ በጠንካራ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ጥረት፡-

  1. በተለያዩ ዓመታት የአትሌቲክስ ዳኞችና አሰልጣኞችን የሙያ ብቃት ለማሳደግ አስፈላጊው የሙያ ማሻሻያ ስልጠና በበቂ ሁኔታ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
  2. በፌዴሬሽኑ የውድድር ዓመታት መጀመሪያ ላይ ይካሄዱ የነበሩትን ከ5 የማይበልጡ ውድድሮች በማስፋት በአሁኑ ጊዜ በዋነኝነት በሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስት አክሲዬን ማህበር ስፖንሰር አድራጊነት ከ1ዐ የሚበልጡ ውድድሮች እንዲካሄዱ በማድረግ የወጣቱ ተሳትፎ እንዲጨምር ተደርጓል፡፡
  3. የፋይናንስ እጥረቱን ለማቃለል እንዲቻል ከስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶችና ከዕርዳታ ሰጪ ድረጅቶች ጋር ተገቢው የስራ ግንኙነት ተፈጥሯል፡፡
  4. የኢትዬጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች በመሳተፍ ውጤታማ አትሌቶች ለማፍራት ተችሏል፡፡
  5. ከፍተኛ ተሳትፎና አጥጋቢ ውጤት ላስመዘገቡ ክለቦች፣ ክ/ከተሞች፣ አትሌቶችና ለኮሚቴ አባላት የማበረታቻ ሽልማት እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
  6. ለፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት አስፈላጊው ማቴሪያልና የሰው ኃይል እንዲሟላ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡
  7. በ አሁን ሰዓት ፌደሬሽኑ ራሱን በአዲስ መልክ በማደራጅት ከፍተኛ ስራ እየሰራ ሲሆን